በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ቢሮ ሥር ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሳልጠኛ ኮሌጆች ክፍት የሥራ መደቦች ላይ
ከዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ጀምሮ አሳልጣኞችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 7 /ሰባት/
ተከታታይ የሥራ ቀናት በኦንላይን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ምዝገባ የሚካሄደው በኦንላይ በመሆኑ በአካል ቀርቦ መመዝገብ አይፈቀድም
- ማንኛውም ተመዘጋቢ የናሽናል አይዲ ቁጥር ሊኖረው ይገባል
- የመረቂቂያ ውጤታቸው ለሁለቱም ፆታ 3.00 ነጥብና በላይ ያላቸው ብቻ መመዝገብ ይችላሉ
- ቅጥር ተፈጽሞ ስራ ከጀመሩ በኃላ የማሰልጠን ስነ-ዘዴ ስልጠና (TM) በመሰልጠን መብቃት እና የአሰልጣኝነት ሰርቲፊኬት መያዝ
የሚጠይቅ መሆኑን ፡፡ - በሙያ ብቃት ምዘና (COC Holistic) መብቃት ወይም ብቁ መሆን የሚጠይቅ መሆኑን፡፡
- ሴት አመልካቾች ወይም ተወዳደሪዎች እናበረታታለን